የ 5 ሳምንታት ነፍሰ ጡር: የሕፃን መጠን, ምልክቶች, ምን እንደሚበሉ እና ጠቃሚ ምክሮች
የመጀመሪያ ሶስት ወር እርግዝና
ልጅዎ እንደ የብርቱካን ዘር ያክላል
የህፃን እድገት
Main Topics
ዋና ነጥቦች
የመጀመሪያው አልትራሳውንድ!
ይህ የመጀመሪያዎ የቅድመ ወሊድ የሆስፒታል ጉብኝት ይሆናል እና ይህ የመጀመሪያዎ አልትራሳውንድ ሊኖርዎት ይችላል በዚህ ጉብኝት ወቅት። በሚቀጥለው ሳምንት የልጅዎ ልብ መምታት ሊጀምር ይችላል፦
ጠቃሚ መረጃ
እርግዝናዎ ስለተረጋገጠ፣ እንደ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ጥቂት ምልክቶች ስላለዎት ከፈለጉ ለቅርብዎ እና ለምትወዷቸው እርጉዝ መሆናቹ መናገር ይችላሉ።
የእርግዝና ወሳኝ ደረጃ
በ ሳምንት 5ሁለተኛ ወርዎ ላይ ነሽ!
የልጅዎ እድገት
ሳምንት 5
የፅንሱ እድገት
ልጅዎ ምን ያህል ትልቅ ነው?
በ 5 ኛው ሳምንት የወር አበባዎ አልፏል እና እርግዝናን በቤት ውስጥ የእርግዝና ምርመራዎች ማረጋገጥ አለብዎት።
ህጻኑ በማህፀን ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የማህፀን ሐኪም መጎብኘት ጊዜው ነው። አሁን ልጅዎ በጠንካራ ሁኔታ እያደገ እንደ ታድፖል ይመስላል፦
ክብደት
0.1 g
ርዝመት
0.34 cm
የብርቱካን ዘር መጠን ያክላል
የእናት የሰውነት መለወጥ
ምን ይቀየራል?
በዚህ ወቅት፣ መለስተኛ የአካል አልመመችት ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። አካልሽ ትንሹን ልዑል ወይም ልዕልት ለመንከባከብ እና ለማዳበር በሚዘጋጅበት ጊዜ ነው።
መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ዑደት ያላቸው ሴቶች እነዚህ ምልክቶች በእርግዝና ምክንያት መሆናቸውን ላያውቁ ይችላሉ እና እርጉዝ መሆናቸው ለማወቅ ጥቂት ተጨማሪ ቀናት ይፈጅባችዋል።
ማወቁ ጥሩ ነው!
የእርግዝና ምልክቶች
አታስቢ። ብዙ ሴቶች በዚህ ሳምንት እስካሁን ምንም ነገር አይሰማቸውም። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ እርግዝና ምልክቶች እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ አይጀምሩም
ውጥር ያለ ጡቶች
ይህ አብዛኛውን ጊዜ ከመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ምልክቶች አንዱ ሲሆን ከ 4 እስከ 6 ሳምንታት ይጀምራል እና እስከ መጀመሪያው ሶስት ወር መጨረሻ ድረስ ይቆያል.
ድካም
ብዙ ሴቶች ድካም ሊሰማቸው ይችላል ግን ለሌሎች ሴቶች የባሰ ጥንካሬ ሊሰማቸው ይችላል
ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ
ሞርኒግ ሲክነስ የማይታወቅ አይደለም። ልክ እንደ 4 ሳምንታት ሊጀምር ይችላል ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ወደ 6 ሳምንታት አካባቢ ይታያል
በተደጋጋሚ የሽንት መሽናት
ይህ በማህፀን ውስጥ እየጨመረ በሄደ መጠን እንዲሁም በሰውነት ውስጥ የሆርሞን ለውጦች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
ከመጠን በላይ የሆነ የምራቅ ፈሳሽ
ምንም እንኳን ከመጠን በላይ ምራቅ በጣም የተለመደ ምልክት ባይሆንም፣ ሞርኒግ ሲክነስ የሚሰማቸው ሴቶች አሁንም በአፍ ውስጥ ምራቅ ሲከማች ሊሰማቸው ይችላል።
የስሜት መለዋወጥ
በእርግዝናዎ ጊዜ ሁሉ የስሜት መለዋወጥ ሊያጋጥምዎት ይችላል። እነዚህ የስሜት መለዋወጥ አብዛኛውን ጊዜ ከ የወር አበባ ጊዜ የነበሩት ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው።
የምግብ አምሮት እና ጥላቻ
እንደገና በሰውነት ውስጥ በሆርሞን ለውጦች ምክንያት፣ ብዙ ሴቶች ይህንን እንደ መጀመሪያ ምልክት አድርገው ይመለከቱታል። ሞርኒግ ሲክነስ ወይም ማቅለሽለሽ ወደ ምግብ ጥላቻ የበለጠ ሊያመራ ይችላል።
የልጅዎ ቅርጽ
የእርግዝና ምክሮች
- ጥሩ ስሜት ላይ ይሁኑ እና ጭንቀትን ይቀንሱ
- ቫይታሚኖችን እና ማሟያዎችን (ፎሊክ አሲድን ጨምሮ) መውሰድዎን ይቀጥሉ።
- በእግር ይራመዱ እና እንቅስቃሴ ላይ ይቆዩ
- ቅድመ ወሊድ ቀጠሮዎችን ያድርጉ
- የባለቤጽሽ እርዳታ እና ድጋፍ ይጠይቁ
መግዛት ያለባቹ ነገሮች
-
Reverse Withdrawal Payment">
-
Onesies">
-
Swaddle">
-
Baby bottle">
-
Stroller">
-
Voyage Yoga Bag">
-
Impulse Duffle">
-
Fusion Backpack">
-
Rival Field Messenger">
-
Onesies
Br50.00Add to WishlistAdd to cartAdd to Wishlist -
Stroller
Br32.00Add to WishlistAdd to cartAdd to Wishlist -
Sale!
Baby bottle
Br25.00 – Br30.00Add to WishlistSelect options This product has multiple variants. The options may be chosen on the product pageAdd to Wishlist -
Swaddle
Br33.00Add to WishlistAdd to cartAdd to Wishlist
Add a Comment